ጥቂት ቃላት ራስን ስለመሆን . .
[ ስብእና ፩ ፥ ካርል ዮንግ ] . . .
አሁን አሁን በየአደባባዩ የሚሰበከዉ ራሳችሁን ሁኑ ነዉ.። መቲቬተሩ ፣ ሰባኪዉ ፣ ቲክቶከሩ. . . እንደቀላል የሚወረዉረዉ ምክር ሆኗል።
ነገር ግን እንደሚባለዉ ራስን መሆን ቀላል አይመስልም። ሰዎች አይደለን ዉስብስብ ፍጥረት ነን። የምንሆነዉ አንድ እዉነተኛ ማንነታችንን ማወቅ ከባድ ብቻ ሳይሆን ሲበዛ አታካች ነዉ። ለምን? ብዙ እኛ ነን ብለን የማናምናቸዉ ፥ እኛም የማናዉቃቸዉ ማንነቶች ይኖሩናል። ደግሞም የማህበርሰብ ዉጤት እንደመሆናችን ባህልና ከባቢያችን ማንነታችን ላይ ትልቅ ጥላ ያሳርፋ። እናማ ጥያቄዉ የቱ ነዉ እዉነተኛ ማንነታችን ይመስለኛል። እኛ ነን ብለን የምናምነዉ ወይ ሰዎች ናቹህ የሚሉን ወይስ ከዛም የሚሻገር ማንነት አለን ?
ብዙ ሰዉ ራሳችሁን ሁኑ ወይም ራስን መሆን ሲል እዉነተኛ ማንነትችሁን ሁኑ ለማለት ይመስላል። ስላሉን አብዛኛዉ ማንነት እና ባህሪዮቻችን ግን ጠንቅቀን አናዉቅም። ከእኛ እዉቅና ዉጪ የሆኑ ብዙ ባህሪ እና ምንነቶች አሉን። ራስን መሆን ማለት ይሄን ከእዉቅናችን ዉጪ ያለዉ ስብእናችንን መረዳት ነዉ ይላል ኦስትሪያዊዉ አናሊቲክ ሳይኮሎጂስት ካርል ዮንግ። የፍሮይድ ደቀመዝሙር የነበረዉ በኋላም የራሱን የስነልቦን መንገድ የቀየሰዉ ዮንግ አዮን በሚለዉ መጽሃፉ ራስን መሆን ማለት ከእዉቅናችን ዉጪ ያሉ የእኛ የሆኑ ማንነቶችን መረዳት እና ማዋሃድ ስንችል የምንደርስበት መንገድ ነዉ ይላል። ይሄንንም Individuation process ይለዋል ፥ ራስን የመሆን ሂደት እንደማለት።
“Individuation means becoming an “in-dividual,” and, in so far as “individuality” embraces our innermost, last, and incomparable uniqueness, it also implies becoming one’s own self. We could therefore translate individuation as “coming to selfhood” . . .”
Carl Jung, Two Essays in Analytical Psychology
ዮንግ በእዉቅናችን ስር ያለዉ ስብእናችን ኢጎ እና ፐርሶና የምንላቸዉ ማንነቶችን አሉት ይላል። EGO /ኢጎ እኛ ነን ብለን የምናሰዉ ማንነት ሲሆን ሃሳብ ፣ ትዉስታ ፣ ስሜቶቻችንን ያቀፈዉ እኔ ብለን ስንናገር የምናመለክተዉ ( Imply) የምናደርገዉ ማንነት ነዉ።። ከሶስት አራት አመታችን ጀምሮ መዳበር የሚጀምር ሲሆን ወጥ የሆነ ማንነት አይደለም። በየጊዜዉ የሚያድግ ፣ የሚቀነስ ፣ የሚጨመር ማንነት ነዉ። የምንወደዉ የምንጠላዉ ፣ አቋም ፣ ባህሪዎቻችን ስለሚቀያየሩ እኛ ነን ብለን የምናስበዉ እኛነት ይሄ “ኢጎ ያልነዉ” በየጊዜዉ ይቀያየራል።
Persona ደሞ ቀባብተን በአደባባይ የምናቀርበዉ ማንነት ነዉ። ማስክ የለበሰ ኢጎችን በሉት። የቃሉ ቀጥተኛ ፍቺ ራሱ (in Latin) ሮማዉያን አክተሮች የሚለብሱት ማስክ ማለት ነዉ። ፐርሶና ማህበረሰብ እና አከባቢያችን ናቹህ ብሎ እንዲያስበን የምናሳየዉ ማንነት ነዉ። ለመወደድ ፥ ለመከበር ፥ ተቀባይነት ለማግኘት ሊሆን ይችላል። የእኛነታችንን ነጸብራቅ የሆነ መጠን ሊይዝ ይችላል ነገር ግን እዉነተኛ ማንነታች ነዉ ማለት አይደለም። ፐርሶና ባጠቃላይ መጥፎ ወይም የማይጠቅም ማንነት ነዉ ማለት አይደለም። አንዳንድ ሁኔታ እና አከባቢዎች የሆነ አይነት ማንነት መያዝ ያስገድዱናል። Persona ችግር የሚሆነዉ ከአንድ ነጠላ ማንነታችን ወይ የሆኑ ሰዎች ናቹህ ብለዉ ከሚያሙኑን ማንነት ጋር ራሳችንን ፍጹም ስናስተሳስር ነዉ። ሰዉ ዉስብስብ ፍጥረት አይደል አንድ ነጠላ ማንነት ሙሉ እኛነት ሊሆን አይችልም።
ሌላዉ ደግሞ ከእዉቅናችን የተደበቀዉ ሻዶ ወይም ጥላ ስብእናችን ነዉ። እዚህ ጋር የዮንግ ሃሳብ ከፍሮይድ የሚለየዉ ዮንግ የግላችን የሆኑ የዘነጋናቸዉ ፥ ማስታወስ የማንፈልጋቸዉ ትዉስታ እና ስሜቶች ብቻ ሳይሆን ከትዉልድ ትዉልድ የወረስናቸዉ ጥንታዊ እዉቀቶችን የያዘ ክፍል አለን ይላል። Collective Unconscious የሚለዉ ። ይሄ ሃይማኖታዉ መገለጦች ፥ ምልክቶችን ( Archetype) የያዘ ክፍል ነዉ ይለናል። በተላያየ አካባቢ እና ትዉልድ ማሃል ተፈጥን እንኳን የሰዉ ልጆች ተቀራራቢ ህልም አፈታት ፥ እምነታዊ ምልክቶች ፥ ኮኮብ ንባቦች ያለን ለዚን ነዉ ብሎ ያስረዳል። ስለዚህ ሌላ ጊዜ በሰፊዉ እናያለን ለአሁን ስለ ግለሰባዉ ስለሆነዉ ጥላ ማንነት ወይም Personal Shadow ብቻ በጥቂቱ እንይ . . .
ይሄ ጥላ (Shadow) የምንለዉ ማንነት የስብእና አካል ከልጅነት ጀምሮ የዘነጋናቸዉ ፥ ማስታወስ የማንፈልጋቸዉ ትዉስታ እና ስሜቶችን ጥርቅም የእዉነተኛ ማንነትችን ጥላ ማንነት ነዉ። መጥፎ ፥ የከፉ ባህሪያት ጥርቅም ብቻ ሳይሆን በከባቢያዊ ምክንያቶች የተገፉ በጎ ድርጊቶችንም የያዘ ሊሆን ይችላል። መገለጫዎቹን አይተን ጥላ ስብእናችንን ወደ እዉቅናችን ለማምጣት ከሞከርን Shadow ትልቅ አቅማችንን (Potential) የያዘ ማንነት ነዉ። ችላ ካልነዉ ግን እለት በእለት አደገኛ ይከፋል። ምክንያቱ በየእለቱ እየቀበርናቸዉ ፥ በየቀኑ እየካድናቸዉ የምንሄደዉ ስሜቶች ፥ ትዉስታዎች ይኖንሩናል ሞልተዉ ፍሰሱ ቀን የሚያጥለቀልቁን።
"The shadow is a living part of the personality and therefore wants to live with it in some form."
'Until you make the unconscious conscious, it will direct your life and you will call it fate .' C.G. Jung
እንደያንግ እዉነተኛ ማንነታችን እነዚህን ሁሉ ኡሉንም ያቀፈ የተዋሃደ ማንነት መገንባት ስንችል ነዉ። ያን ሂደት ነው የindividuation ያለዉ መድረሻዉን ደሞ ( የተሟላዉን ማንነት ) The Self ይለዋል።
ራስን መሆን እንዴት?
ዮንግ ራስን ለመሆንም መሰረታዊ የሚላቸዉ ብዙ ሂደቶች አሉ ከጊኢዘም ከእዉቀትም አንጻር እኔ ሶስቱን ሃሳቦች ላካፍላቹ።
የመጀመሪያዉ ጠንካራ ኢጎ መገንባት ነዉ።
አሁን አሁን በብዛት ኢጎ እንደችግር ሲጠቀስ እንሰማለን። አደገኛዉ ግን ትልቅ ኢጎ ሳይሆን ደካመ ኢጎ መያዝ ነዉ። ኢጎ እኛ ነን ብለን የምናስበዉ ማንነት እስከሆነ አንድ ሰዉ ነኝ ብሎ የሚያምንበት ጠንካራ ማንነት ከሌለዉ ስለራስ ጠንካራ መረዳት (Strong sense of self) ሊኖረዉ አይችልም። ያኔ የእሱነቱ መገለጫ ፐርሶናዉ ይሆናል። ኢጎን ለመሻገር መጀመሪያ ኢጎ ሊኖረን ይገባል። ለዛ ነዉ አንዳንድ ሰዉ ዉያዉ ፣ ዝናዉ ወይ ስልጣኑ የእሱ እዉነተኛ ማንነቱ እንደሆነ የሚሰማዉ። ያ ፐርሶና የተጠቃ የመሰለዉ ጊዜ ቁጡ (defensive) ብሎም አደገኛ ይሆናል። እንደ ያንግ ሁሉም ሰዉ እስከእድሜዉ አጋማሽ በብዛት እስከ 35 አመት ኢጎዉን የማዳበሪያ ዘመኑ ነዉ ይለናል። ወጣትነት ላይ እኛ ነን ብለን የምንገልጸዉ ማንነት መገንባት አለብን ይላል። ማንም እኔ እንዲህ ነኝ እንዲህ አምናለሁ ማለት ሳይችል ራስን ማመን ፥ ራስን ማክበር ከየት ይመጣል።
“If you sum up what people tell you about their experiences [on the path of individuation], you can formulate it this way: They came to themselves, they could accept themselves, they were able to become reconciled to themselves, and thus were reconciled to adverse circumstances and events.”
ሁለተኛዉ self - reflection ነዉ። ሃሳብ ፥ ስሜት ፥ ባህሪዎችችንን መመርመር መቻል። ሰዉ ልጅ ራሱን እንደሚዋሽ ሌሎችን አይዋሽም። ነገሮችን ስለምን እያደረግን እንዳለን ከማወቅ ዉጪ ምርጫ የለንም።
“[W]isdom begins only when one takes things as they are. . .So it is a healing attitude when one can agree with the facts as they are. . .only then can we thrive.”
Carl Jung, Visions: Notes of the Seminar Given in 1930–1934, Vol. I
ሶስተኛ ፍርሃትን መጋፈጥ ነዉ። ከፍርሃትህ ጀርባ የተደበቀ ሽልማት አለ። ሁሌም የሆነ የምንፈራዉ ግን ማድረግ እንዳለብን የሚሰማን ነገር ይኖራል። አዉቀን ግን ፈርተን ወደ ጎን የምንገፋዉ። ዉጫዊ ብቻ ላይሆን ይችላል። ዉስጣዊም ያለፈ ፥ ማስታወስ የምንፈልገዉ ፥ የምንፈራዉ ትዉስታና ጊዜ ካለ ያን በመጋፈጥ ፥ በመሻገርም ነዉ ራስን የማወቂያ ፥ የማግኛም መንገድ። አቅማችንን ልክ በብልቃጥ ዉስጥ እንደታጠረ ጂኒ ብታስቡት አንድ ፍርሃት መጋፈጥ የሆነ አቅማችንን ከብልቃጧ እንደማዉጣት ነዉ። ብዙ ፍርሃትችንን በተጋፈጥን ቁጥር የበለጠ አቅማችን ከእግረሙቅ፥ መሻታችን ከእስር እያወጣን እንሄዳለን።



በጣም አመሰግናለሁኝ ።ስለ ፡እንደዚህ ፡ዓይነት ፡ርዕሶች ፡ማንበብ ፡አዘወትራለሁ፡እና ፡በአማርኛ ፡ስላገኘሁት፡ደስ ፡ብሎኛል ። I have been reading Sigmund Freud and Carl Jung's works for some time.